ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬዲዮ መስከረም 23 ቀን 2000 ዓ.ም ሥራ የጀመረ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ የግል ኤፍ ኤም ሬዲዮ ጣቢያ ነው፡፡
ይህ ከአዲስ አበባ በ250 ኪሎ ሜትር ክበብ ውስጥ ፕሮግራም እንዲያሰራጭ ፈቃድ አግኝቶ የረጅም ጊዜ የሬዲዮ ሥራ ልምድ ባላቸው ባለሙያዎች የተቋቋመው ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬዲዮ በአጭር ጊዜ ውስጥ በአድማጮች ዘንድ ተወዳጅነትን ሊያተርፍ ችሏል፡፡
ሸገር 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡ የሸገር ዓላማ ከወገናዊነት የነፃ ትክክለኛ የሕዝብ ድምፅ መሆን፣ ሥነ ምግባርን የጠበቀ የጋዜጠኝነት መርህን መከተልና የተሣካለት የኢንፎቴይመንት (information & entertainment) ሬዲዮ ጣቢያ መሆን ነው፡፡
ጣቢያችን ለማንም ባለመወገን ለሁሉም በታማኝነትና በመልካም ሥነ ምግባር መልካም አገልግሎት በመስጠት የሚያምንና ለእነዚህም እሴቶች ትልቅ ክብር የሚሰጥ ሬዲዮ ጣቢያ ነው፡፡
ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር! ... read more
Welcome to the new Streamitter website. We have improved the online radio experience for you. Enjoy listening to thousands of radios all over the world.
  2004 - 2025 Streamitter.com